Gaaffii 1
አንድ የተማረ ሰውና አንድ ያልተማረ ሰው በጀልባ ሲሄዱ ትልቅ አውሎ ነፊስ ተነስቶ ጀልባውን ሊገለብጠው ከወዲያና ከወዲህ እያንገላታ በጣም የሚያስፈራ ሆነ፡፡ አዋቂው ሰውዬ በዙህ ጊዛ እጆግ ፈርቶ ተንቀጠቀጠ፡፡ ያልተማረው ግን ምንም ሳይፈራ ጀልባ እንዳይገለበጥባቸው ከማዕበሉ ጋር እየታገለ ከብዘ ጭንቅ በኋላ በደህና ወደ ጠረፍ ወጡ፡፡ ያልተማረው ሰውዬ በጣም እየሳቀ አየው፡፡ “የኛ ሊቅ እኔ ‹ያልተማረ› የተባልኩ ሰው ምንም ሳልፈራ አንተ ግን የተማርክ፣ ብዘ ነገር ታውቃለህ የተባልክ ሰው ይህንን ያህል በፍርሀት ስትንቀጠቀጥ በማየቴ እጆግ አድርጎ አሳቀኝ፡፡” እያለ አሾፈበት፡፡ ሰውየው ተናዶ “አንተ ያልፈራህበት ምክንያት ብትኖርም፣ ብትሞትም ለዓለም ምንም የምታጎድል የሌለ መሆኑን ስለምታውቅ ነው፡፡ እኔ ግን ብሞት ለአለም ብዘ ነገር እንደሚጎድል አውቃለሁና ለዙህ ነው ሞትን በጣም አድርጌ መፍራቴ”አለው፡፡ ምንጭ፡- ከበደ ሚካኤል፡ ታሪክና ምሳሌ 1ኛ መፅሐፍ 1948 ከላይ የቀረበው ምንባብ ርዕስ ምን ሊሆን ይችላል?
- A.ጀልባ
- B.የተማረ ሰው መልስ
- C.አውሎ ነፊስ
- D.ያልተማረ ሰው መልስ
Deebii fi ibsa ilaalaa
Deebii: B የተማረ ሰው መልስ
Maaliif