Question 1
ምንባብ አሊ አምስት ዓመት እንኳን ሳይሞላው ነበር የሞቱት፡፡ በአብዛኞቹ የገጠር ልጆች ላይ እንደሚሰራው ሁሉ አሊም እረኝነት እጣው ፈንታው ሆነ፡፡ አንድ ቀን አሊ አጭር ግራር ሥር በሐሩር ጉልበት ተሸንፎ በራበው ሆዱ ተኝቶ ሳለ ከጆሮው ራቅ ወደጆሮው ቀረብ ራቅ ቀረብ የሚል ደስ የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ ከሚያንጎላጅበት ቀና ሲል ድምፁ የሚመጣበትን አንድ ሸማግሌ ገበሬ የሚኖሩባትን አንዲት ደሳሳ ጐጆ ፈትለፊቱ አየ፡፡ አንዴ ቆም ብሎ እየሰማ አንዴ ወደ እሳቸው እየተጠጋ ቆሞ እያዳመጠ ወደ ጎጆዋ እየተጠጋ እየቆመ እየተራመደ ፊታቸው ተገተረ፡፡ በቀኝ ክንዳቸው ስር የሸጎጡዋትን ጥቅርሻ የለበሰች ክራር እየገፋ ቀና ብለው በትናንሽ አየኖቻቸው አዩት፡፡ አሊም በፀሀይ ግለት ያብረቀረቀ የጠቆረ ፊቱን እያሸ ሸማግሌው እግር ስር ቁጭ አለ፡፡ የጰጰስ ቆብ መስሎ ከተራሮች መኸል የጎላ ተራራ ሆኖ ጠፍጣፋ ምድር ላይ የተተከለው ዳዲሞስ እየመሸ ሲሄድ ግዝፊቱና ግርማው መታየቱ ቀርቶ እየሟሟ ሲጠፋ የሽማግሌው ድምፅና የክራር ግርፍ ብቻ አካባቢውን ዋጠው ፡፡ በአንድ ክንዱ ተደግፎ አቦ "ፋርጤን ፊታቸውንና ሁኔታቸውን በአይኑ እይቃኘ ሲያዳምጥ "መሸብህሒድ! በጎችህም እንዳይጣፋብህ" አሉትና በአንድ እጃቸው ራሱን ዳበሱት፡፡ አሊ በክራር ፍቅር ያኔ ነበር የተለከፈው፡፡ ምንጭ ኤክስትሪም አማርኛ 5-8 ክፍል የተወሰደ • አሊ እናቱን በሞት ያጣው መቼ ነው?
- A.በአንድ ዓመቱ
- B.በሁለት ዓመቱ
- C.በሶስት ዓመቱ
- D.አምስት ዓመት ሳይሞላው
Show the answer and explanation
Answer: D አምስት ዓመት ሳይሞላው
Why