Question 1
ፈረስ እንደ ጦር መሳሪያ የሚቆጠር የጀግና ጓደኛ ነበር።። አባቶቻችን ጎራዴ ታጥቀው ፤ ጋሻ አንግበው ፤ ጦር ሰብቀው በየጦርነቱ እየዋሉ ጠላትን የጠበቁትና ሀገር ያቀኑበት እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል።። የጥንት ወታደሮች እንደ ዛሬው መንገድ ሳይኖር ፤ መጓጓዥ ሳይመቻና ሳይቀለጥፍ ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ይዘዋወሩ የነበቱት እንደ ፈረስ በለ ጋማ ከብት ነበር።። በጦርነት ጊዜ ፈረስ ጀግናን በስሙ በማስከበሩ ሌላ በሰላም ጊዜም በመጓጓዥነት ሲጠቅም የኖረ ታማኝ አገልጋይ ነው።።ፈረስ ተቀማጩን ብቻ ሳይሆን የጌታውን ሚስት ፤ የጌታውን ልጅ በአጠቃላይ የጌታውን ዘመድ አዝማድ ሁሉ የሚያኮራ እንሰሳ ነው።። በዚህም የተነሳ ቀደም ባለው ጊዜ በአገራችን በፈረስ ስም መጠራት የተለመደ ነበር።። ፈረስ በተቀመጡበት ጊዜ የልብ የሚያደርስ ፤ ጌታውንም የሚያኮራ እንደመሆኑ መጠን ጥንቃቄ ሊደረግለት ይገባል።። ስለዚህም ከአኗኗሩ ምቾት አግኝቶ ምግብም መጠጥም እንዳይጓደልበት ለብቻው ተገልሎ ሲቀለብ እጅግ ከፍ ያለ ሀይል እየተሰማው ይሄዳል ጉልበቱም ብርታትና ንቃትም ይኖረዋል... (ማህተመስላሴ ቼ በለው ፤ 1961፤9-11) ምንባቡ በስንት አንቀጽ የተገነባ ነው?
- A.በሦስት
- B.በአራት
- C.በሁለት
- D.በአንድ
Show the answer and explanation
Answer: C በሁለት
Why